ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎች (Smart classes) ስራ ያለበት ደረጃ ምልከታ ተካሄደ፡፡

University News

(ታህሳስ /2017 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራን በቴክኖሎጅ የታገዘ ለማድረግ በሁለቱም ግቢዎቹ ያሰራቸውን ዘመናዊ (Smart Classroom) መጠናቀቅ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲው ሃላፊዎች፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችና በደሴ ድስትሪክት የቴሌኮሙኒኬሽን የስራ ሀላፊዎች ያለበት ደረጃ ምልከታ ተካሂዷል፡፡
በምልከታውም ወቅት ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች (Smart classes) ስራው ተጠናቆ ለስራ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር) እንደተናገሩት ከቴሌኮሙኒኬሽን ሃላፊዎች ጋር ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎች (Smart classes) ስራው ያለበትን ደረጃና በቀጣይ በጋራ የሚሰሩ የስራ አቅጣጫ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የመረጃ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት መምህር አብርሃም በለጠ በበኩላቸው እንደተናገሩት (Smart classes) ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና የመማር ማስተማር ስራውን በማዘመን አሰራርን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረዎጃች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *