የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡.

University News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡.

(የካቲት 8/2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሁለቱም ካምፓስ አመራሮች፣መምህራንና የአስተዳር ሰራተኞች በተገኙበት ከዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ጋር በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ና እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ እንድሁም ከበርዱ የስራ እንቅስቃሴዎች አኳያ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱም ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በስራ አመራ ቦርዱ በኩል መሰራት አለባቸው ያሏቸውንና መደገፍ የሚገባውን ጉዳዮች በጥያቄ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የስራ አመራር ቦርዱም በበኩሉ እስካሁን ባለው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲውን ከማጠናከር አንፃር የተሰሩ ስራዎች ውስንነት መኖሩን ገልፆ በቀጣይ በሙሉ አቅሙ ተቋሙን ለመደገፍ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

ለለውጥ እንተጋለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *