መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ( march 8 ) በተለያ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
( መጋቢት 4/2016 ዓም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት) በአለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሃገራችን ለ48ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዩኒቨርሰቲያችንም ለ6ኛ ጊዜ ‹‹ ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 4/2016 የዩኒቨርሲቲው መምህራን አስተዳድር ሰራተኞች ተማሪዎች እንድሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሴቶችን የሚያበረታቱ ስነጽሁፎችና ንግግሮች ቀርበው ዕለቱን በደመቀ ሁኔታ እንድከበር ተደርጓል ፡፡ ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ሰብለወርቅ አበበ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹March 8>>የሚከበረው ሴቶች ከወንድ አጋሮቻችን ጋር እኩል የመሳተፍ ፣የምስራት አቅም እንዳላቸው በግቢያችን ያሉ ሴት ተማሪዎች በተሳትፎም ሆነ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ማስመዝገባቸው የዚህ ትግል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ይህ ቀን የሴቶችን የስርአተ -ጾታ እኩልነት የሚረጋገጥበትና ሴቶች በሴትነታቸው ሊያግዳቸው የሚችል ነገር እንደሌለና እኩል ተሳታፊ መሆን እንደሚችሉ የሚያረጋግጡበት ቀን ነው ብለዋል ፡፡
ይህንን ዕለት በአጋርነት አብሮ ያከበረው የአቢሲኒያ ባንክ ቱሉ አውሊያ ቅርንጫፍ‹‹ ሴቶችን ማገዝ ሃገርን ማገዝ ነው›› በሚል መሪ ሃሳብ የዕለቱን ፕሮግራም ሙሉ ስፖንሰር በመሆንና በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 3 ሴት ተማሪወች ለእያንዳንዳቸው የ1000ብር አካውንት በመክፈት ድጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡
በመጨረሻም ተሳታፊወች ‹‹ ሴቶች በዩኒቨርሲቲው ባሉ በተለያዩ ዘርፎች ቢሳተፉ ውጤታማ ከመሆን የሚያግዳቸው እንደሌለ ታሪክ ነጋሪ ብቻ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ መሆን እንደሚችሉ የተማሪወቻችን ውጤት ምስክር ነው››
ለለውጥ እንተጋለን!Striving for change!
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!