የሀገር ፍቅር ለብሄራዊ ማንነት ግንባታ እንድሁም ባህል ፣ አብሮነት ናልማት በሰነ- ቃላዊ ግጥሞች በሚሉ ፅንሰ ሃሳቦች ፅብረቃ ተካሄደ።
( ግንቦት 28/2016ዓም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ና ስነ ሰብ ኮሌጅ ስር በፖለቲካል ሳይንስ እና በአማረኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍሎች የተዘጋጀ የሀገር ፍቅር ለብሄራዊ ማንነት ግንባታ እንድሁም ባህል ፣ አብሮነት ናልማት በሰነ- ቃላዊ ግጥሞች በሚሉ ፅንሰ ሃሳቦች ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች መምህራን የአስተዳደር ሰራተኞች ና ተማሪዎች በተገኙበት በሁለት ርዕሶች ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የሀገር ፍቅር ለብሄራዊ የጋራ ማንነት ግንባታ በመምህር ሀብታም አለምነው የቀረበ ሲሆን ባህል አብሮነት ና ልማት በስነ-ቃለዊ ግጥሞች ላይ በመምህር መሀመድ ሰይድ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በእለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ ሹመት አሰፋ (ዶ/ር) እንደተናገሩት እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም አብሮነትን የሚያበረታቱ ፤ ሀገር በቀል ዕውቀቶች ላይ ጥናት ማድረግ በአካባቢያችን ያሉትን ባህሎች እሴቶች እምቅ ሀብቶችን እንድናውቅ የሚረዳ ሲሆን ከምሁራንም የሚጠበቅ ስራ መሆኑን ጠቁመው መሰል ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል ፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ጽሁፍ መገምገም ብቻ ሳይሆን ነባራዊ የሀገራችን ሁኔታ ላይ እንድንወያይ ሃገር በቀል እውቀቶች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ ፤ብዙ ያልታዩና ያልተዳሰሱ ባህለዊ እሴቶች ስላሉን ጥናት አድራጊዎችን መደገፍ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር) በዚህ አመት ብዙ ሴሚናሮች እየቀረቡ ያሉበትና የተሻለ ስራዎችን እየተከናወኑ ያሉበት አመት መሆኑን ገልጸው ሴሚናሮች መዘጋጀታቸው እንደ ዩኒቨርሲቲ ሃሳቦችን በመግለፅና በመወያየት የመግባባት ሀሳብ መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
እየተፈጠሩ ያሉብንን ችግሮች ለመፍታት ዩኒቨርሲቲወች ትልቅ ስራ መስራት እደሚጠበቅባቸው እና ምሁራን ቀጣይነት ያለው ጥናትና ምርምር በማድረግ ለሃገር የሚጠቅሙ አንድነትን ሊያጠነክሩ የሚችሉ አዳዲስ የመወያያ ሃሳቦች መፍጠር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡