የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ1445ኛውን የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) ባዕልን ከተማሪዎቹ ጋር በደመቀ ሁኔታ አከበረ።

University News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ1445ኛውን የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) ባዕልን ከተማሪዎቹ ጋር በደመቀ ሁኔታ አከበረ።

በዓሉ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የሃይማኖት አባቶች ዋናው ግቢ ቱሉ አውሊያ በመገኘት ከተማሪዎች ጋር በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

በዕለቱ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር) ተማሪዎችበበዓሉ ዕለት ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ከጎናቸው በመሆን እየደገፉ ያሉትን የሀይማኖት አባቶች አመስግነው፤ በዓሉን በጋራ ሆኖ መተሳሰብና ሃይማኖቱ የሚፈቅደውን በጎ ተግባር በማድረግ አክብሩ ብለዋል፡፡በዓሉ የአብሮነት፣የሰላም እና የደስታ እንደሆን ተመኝተዋል፡፡

የሀይማኖት አባቶችም በበኩላቸው እለቱን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል፤ ከተማሪዎች ጋር በማክበራቸውም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *