በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ፣ በአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ትብብር የመጀመሪያ ደረጃ የእግር ኳስ የአሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
(ሰኔ 15 /2016ዓም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራን አዘጋጅነት ከአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር እና ከኢትዮጵያ እግር ፌደሬሽን ጋር በመተባበር facilitating confederation african de football< D> license coaching training for south wollo zone youth football coaches በሚል ርዕስ የመጀመሪያ ደረጃ የእግር ኳስ የአሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው ከሰኔ 15-25/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 11 ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ስለሺ አቢ (ዶክተር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የስልጠናው አላማ የእግር ኳስ የአሰልጣኝነት አቅምን በማጎልበት ሀገር የሚያስጠሩ ወጣቶችን ማፍራት መቻል በመሆኑ ስጠናውን በትኩረት እንድከታተሉ ለሰልጣኖች ያሳሰቡ ሲሆን የሚስፈልጋቸውንም ድጋፍ ለማድረግም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!