ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ ፡፡
=====================================================
ሀምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም (መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት
በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሀምሌ 9-11/2016ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው የ2016 ዓ.ም የሀለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቋል ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳ ሻውል ፈተናው ፍፁም ሰላማዊና በታቀደለት መሰረት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የፈተና አስፈፃሚ ግብረ-ሀይል አባላት፣ የፀጥታ አካላት፣ የጣቢያ ኃላፊዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞች እንዲሁም ተጓዳኝ አገልግሎቶችን አቀላጥፈው በመስጠት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ የተቋሙ ሰራተኞች በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በተለይ የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ላሣዩት የተገባ ድሲፕሊን ምስጋናቸውን አቅርበው በሁለቱም ዙር ለተፈተኑ ተማሪዎች መልካም ውጤት እንድገጥማቸው ተመኝተዋል