3rd National Conference Shaping Sustainable Future: Synergies Between Converging Sciences and Technology

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የነበረው አገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(የካቲት 2/ 2018 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ” shaping sustainable Future : synergies between converging sciences and Technology ” በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን እና ሰራተኞች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ከተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙ ተመራማሪዎች፣የክብር እንግዶች በተገኙበት ከጥር 30 እስከ የካቲት 1/2018 ዓ.ም ለ3ተኛ ጊዜ ሲካሄድ የነበረው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቋል፡፡

በጉባኤው ላይ የሚካሄዱ ምርምሮች የዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫ በሆኑት በግብርና፣በማድን ፣በባህል ፣ በቱሪዝም እና በቴክኖሎጅ የምርምር ትኩረት መሆን እንዳለባቸው የተነሳ ሲሆን በተለይም በግብርናው ዘርፍ ለሚተዳደረው ማህበረሰብ ዘላቄታዊና አካባቢያዊ ልማትን የሚፈጥር፤የቅርስና የአካባቢን ስነምህዳር ለመጠበቅ የሚያስችል፣ የኢኮቱሪዝም ልማትን የሚያሳድግ፣ የተፈጥሮ ማዕድናትን አውጥቶ ለመጠቀም የማያስችል እና ዘመኑ የሚፈልገውን የዲጅታላይዜሽን በመጠቀም ለወደፊት ግስጋሲያችን አስፈላጊ የሆነውን የቴክኖሎጅ ፈጠራ ሀሳብ በማሳደግ የተግባር ጅማሬዎች የሚስፋፈበት እና የምርምር ተግባር ወደ ተጨባጭ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚሸጋገርበት ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተመላክቷል ፡፡

በብዝሀ ህይወት ጥበቃ ስራ ዩኒቨርሲቲው ያለበት አካባቢ መልከዓ ምድራዊ ተፋሰሱ በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ የተመራማሪዎችን ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑም በጉባኤው ተመላክቷል ፡፡

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የምርምር ስራዎችን ያቀረቡ ምሁራን እንዳሉት መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበት አካባቢ የተመራማሪዎችን ርብርብ የሚፈልጉ ያልተሰራባቸውና የምርምር ስራ ቢሰራባቸው ለአካቢቢው ማህበረሰብ ፣ ለሀገር ብሎም ለአለም ተምሳሌትነት ያላቸው ተፈጥሯዊ ፣ሰው ስራሽና ባህላዊ የሆኑ ክስተቶች ያሉበት በመሆኑ የምሁራንን ልዩ ትኩረት የሚፈልግ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምር፣ ሕትመት እና ሥነ-ምግባር ሥርጸት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አገኝ ሽበሺ (ዶ.ር) እንዳሉት የምርምር ኮንፈረሱ ሲዘጋጅ 200 የሚሆኑ የምርምር ጽሁፎች ቀርበው የአካባቢውን ችግር ይፈታሉ የተባሉትን 36ቱ የተመረጡ መሆኑን ገልፀው ለዩኒቨርስተያችን ተመራማሪዎችም ጥሩ ልምድ ያገኙበት ጉባኤ እንደሆነ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ሰዋገኝ አስራት (ዶ.ር) በመድረክ ለተነሱ ሀሳቦችና አስተያየቶች ጠቃሚ መሆናቸውን አመላክተው በቀጣይ ለሚሰሩ ምርምሮች አጋዥ እንደሚሆኑም ተናግረዋል ፡፡

ከተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች የተገኙ ተመራማሪዎችም ለተደረገላቸው አቀባብል ለዩኒቨርሲቲው ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ ለነበራቸው ጥሩ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

ለወቅታዊአናታማኝመረዎጃች:-
Website: https://mkau.edu.et/
Facebook:https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
Twitter:https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn:http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube:https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA
Telegram:https://t.me/+yNhdHU3_pAY0OTM0

Leave a Comment