በመካነ ሰላም ግቢ የተቋሙ የውበትና መናፈሻ አስተባባሪ ወ/ሮ አልማዝ ሙሃመድ እንደገለፁት 1,222 የተለያዩ ሀገር በቀልና ሌሎች ችግኞች በበጋው ወቅት በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ተተክለዋል ብለዋል፡፡ አክለውም በግቢው ውስጥ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የፅድቀት ምጣኔን ለማሳደግ ከዚህ ቀደም ካገኘነው ልምድ ተነስተን መደረግ ያለባቸውን እንክብካቤዎች ሁሉ ሳንታክት እናከናውናለን ብለዋል፡፡
ከወሎ ዩኒቨርሲቲ እና KWF ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ1,100 በላይ የሚሆኑ ሀገር በቀል ችግኞችን በድጋፍ የሰጡ ሲሆን ከነሀሴ1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በግቢው ውስጥ መተከላቸውን የጠቅላላ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አቶ አለሙ ካሳ የተናገሩ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲገመት ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
በሌላ መልኩ የመካነ ሰላም ግቢ የምርምርና ሀገር በቀል እውቀት አስተባባሪ የሆኑት መምህር አያሌው አራጌ እንደ ገለፁት በ2017 ዓ.ም የክረምት ወቅት ከቱሉ አውሊያ ግቢ የምርምር ጣቢያ ተላምደው የመጡ 160 የአፕል ችግኞችም በተዘጋጀላቸው ቦታ ተተክለዋል፡፡

(ነሀሴ 23/12/2017 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት

Leave a Comment