መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ በማኔጅመንት ካውንስል ደረጃ መስከረም 15/2018 ዓ.ም በሁለቱም ግቢዎቹ አካሂዷል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር) ውይይቱን በንግግር በከፈቱበት ወቅት በ2017 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው በቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውል በመግባትና በተዋረድም ለስራ ክፍሎች በማውረድ፣ በጥብቅ ክትትልና ግምገማ በመምራት እንዲሁም የሪፎርም ተግባራትን በትኩረት በመተግበር የላቀ አፈጻጸም አሳይተናል ብለዋል፡፡ ይህ የላቀ አፈጻጸም የተመዘገበውም አመራሩና ፈጻሚው ባደረጉት የጋራ ጥረት በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ጌታሁን ያቀረቡ ሲሆን በ2017 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ውል ከገባባቸው 78 ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች መካከል 71ዱ ከፍተኛ አፈፃፀም እንደተመዘገባበቸው አንስተዋል፡፡ የአመራሩንና የፈጻሚውን አቅም ለማሻሻል ልዩ ዩል ስልጠናዎች መሰጠታቸው ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር ለማቃለል የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ መጀመሩ፣ የሪፎርም ተግባራት አሰራርን በሚያሻሽልና የትምርህት ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ በጥብቅ ድስፕሊን መፈጸም መቻሉ፣ አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞችን ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸው፣ የስራ ግብዓት ወቅቱን ጠብቆ እንዲቀርብ በትኩረት መሰራቱ ወ.ዘ..ተ የሚሉት በሪፖርቱ ላይ በጥንካሬ የተነሱ ናቸው፡፡

የ2018 ዓ.ም ዕቅድም ቀርቦ በዝርዝር ውይይት የተደርገበት ሲሆን ሁሉም አመራር በየደረጃው የስራ ክፍሉን እቅድ የጋራ በማድረግና በመፈራረም እንድፈፅም፣ የስራ ግብአቶች ጥራትና ግዜያቸውን ጠብቀው እንድቀርቡ በማስቻል፣ የውስጥ ገቢን ለማሳደግ የሚያስችሉ አቅሞችን በማሳደግ፣ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን፣ የሪፎርም ስራዎችን በትኩረት ይዞ በመፈፀም በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈፃፀም እንድመዘገብ ሁሉም ሀላፊነቱን በብቃት እንድወጣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አቅጣጫ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ለወቅታዊ አና ታማኝ መረዎጃች:-
Website: https://mkau.edu.et/
Facebook:https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
Twitter:https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn:http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube:https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA
Telegram:https://t.me/+yNhdHU3_pAY0OTM0
ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!

Leave a Comment