(መስከረም 15/2018- ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

ግቢው ሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን ከዛሬ 15/01/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል፡፡ እንደሚታወቀው መካነ ሰላም ግቢ ላለፉት ሁለት ዓመታት በነበርው የጸጥታ ችግር ምክንያት በማስተማር ስራ ለይ አልነበረም።
አሁን ላይ በተፈጠረው መረጋጋት ተቋሙ ተማሪዎችን ከመስከረም 15/01/2018 -16/01/2018 ዓ.ም ድረስ ለመቀበል ባደረገው ጥሪ መሰረት ዛሬ የከተማውና ወረዳው አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ማህበረሰቡ በንቅናቄ ወጥቶ ከአሜጃ አስከ ዩኒቨርሲቲው መግቢያ በር ድረስ በተሽከርካሪዎችና በመልዕክቶች በማጀብና ነጻ ሰርቪስ በመስጠት ተማሪዎችን በድምቀት ተቀብሏል።

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ግቢ ኢክስኪቲቭ ዳይሬክተር አቶ አብዱሮህማን አወል አቀባቀበሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ የመካነ ሰላምና አካባቢው ህዝብ ላሳዩት ታላቅ ትብብርና ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ተማሪዎችንም ^^ከቤተሰቦቻችሁ ወደ ቤተሰቦቻችሁ እንኳን በሰላም መጣችሁ^^ ብለዋል።

የተማሪዎችን በድምቀት የመቀበሉ መርሃ ግብሩ ነገም የሚቀጥል ሲሆን አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች በተደረገላቸው አቀባበል በእጅጉ የተደሰቱ መሆኑን አንስተው የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛና የከተማው ህዝብ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመንፈስ ከእኛ ጋር የቆየና እስከምንመለስም በታላቅ ጉጉት እየጠበቀን እንደበበር የተረዳንበት ከመሆኑም በላይ ይህ አቀባበ ለዓላማችን መሳካት ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

Leave a Comment